|
የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አመሰራረት
የሀረር ከተማ መዘጋጃ ቤት ከሌሎች የሀገሪቱ የከተሞች ማዘጋጃ ቤቶች ጥንታዊና ቀደምትነት ያለው ነው። የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ1933 ዓ/ም ከአዲስ አበባና ከአሰበተፈሪ ማዘጋጃ ቤቶች ጋር በአንድ አመት ውስጥ እንደተመሰረቱ አንዳንድ ምንጮች ሲያመለክቱ የመጀመሪያው የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ህንጻ የአሁኑ መዘጋጃ ቤት ህንጻ ሲሆን ይህም ህንጻ ቱርኮች እንደገነቡት ይነገራል ፡፡
የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ1933 ዓ/ም በንጉስ ኅይለ ስላሴ ዘመን በተቋቋመ ጊዜ የመጀመሪያ የሀረር ገዥና የማዘጋጃ ቤት ሹም በሚል የስልጣን ማዕረግ የተሾሙት የደቡብ ወሎ ተወላጅ የሆኑት ቀኝ አዝናማች አስፋው አሊ ሲሆኑ እስከ ዘውድ አገዛዝ ውድቀት ድረስ ከስድስት ያላነሱ ሹማምንቶች የሀረር ከተማ ገዥና የማዘጋጃ ቤት ሹም በመሆን አገልግለዋል።
የሀረር ከተማ ማዘጋ ቤት በደርግ ዘመን እስከ 1975 ድረስ በዚህ እንጻ ሲገለገል ከቆየ በኋላ ህንፃውን በፕላንና ቀጠና ጽ/ቤት በማስረከብ የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ወደ በህልና ስፖርት ቢሮ እንዲሸጋገር ሲደረግ ከተወሰነ አመት ቆይታ በኋላ በ 1978 ዓ/ም ወደ ዋናው የአሁኑ ህንጻ እንዲመለስ ተደርጎ እስካሁኑም የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በዚህ ህንጻ እየተገለገለ ይገኛል።
በአጠቃላይ ከ1933 ዓ/ም እስከ 2002 ዓ/ም የተሾሙት ሹሞች ብዛት 28 ሲሆኑ በእያንዳንዱ የሹመት ዘመን በርካታ መሰረተ ልማቶች ተከናውነዋል።
በቅርብ ቀን ሙሉ መረጃውን ከዌብሳይታችን ያገኙታል።
|