.
Sunday, 20th May 2012
6:47:06pm
የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2002 የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ያቀረበው እቅድ በምክር ቤቱ ፀደቀ Print E-mail
Friday, 04 December 2009 19:54
 የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 በጀት አመት የልማትና የመልካም አሰተዳደር ስራዎች መሪ ዕቀድ ለምክር ቤቱ አቅርቦ ያስገመገመው ሲሆን በፌደራል የከተሞች ፖሊሲና ፕሮግራምን መሠረት በማድረግ ክልሉ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመቃኘት እንደዚሁም የቱሪዝም ማዕከልነቷን ባገናዘበ መልኩ የመሰረተ ልማት ዕቅድ እየተሰራ መሆኑ በሪፖረት ተገልፆል።

ማዘጋጃ ቤቱ ከተሠጠው ተግባርና ኃላፊነት በመነሳት የተለያዬ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ማዘጋጀቱንና የተዘጋጀውን እቅድ ከተማዋ ጥንታዊነቷንና የቱሪስት መዳረሻነቷን በጠበቀ መልኩ የከተማ ግንባታ ማድረግ ዋነኛው ዓላማ ነው፡፡ በመሆኑም መሠረተ ልማቱን ለማፋጠን የመንገዶች መመቻቸት እና መሠራት ዋነኛ የእድገት በር በመሆኑ በእቅዱ ትልቅ ትኩረት ተሠጥቶታል።

ከዚህም በተጨማሪ አካባቢን ንፁህና ሳኒቴሽንን ጨምሮ የገበያ ማዕከላት የከተማዋን የመሬት ፕላን ስርዓት ማሻሻያ ፕሮጀክት በእቅዱ ተካቶ ቀርቧል፡፡

በ2002 የበጀት ዓመትና የልማትና የመልካም ስራዎች አፈፃፀም ሒደት ላይ በከንቲባ ኮሚቴና በምክር ቤቱ ፀድቋል፡፡
 
HomeNewsGeneral News /  የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2002 የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ያቀረበው እቅድ በምክር ቤቱ ፀደቀ

 Site Visited

  98319 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM