| በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 የመጀመሪያ ሩብ አመት ሪፖርት ቀረበ |
|
|
| Saturday, 05 December 2009 20:02 |
|
በመልካም አስተዳደር እና መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችለውን መሪ እቅድ በማዘጋጀት በከተማው ሁለንተናዊ እድገትና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጅምር ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የ2002 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት አቅርቧል፡፡
በ2002 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከተከናወኑ ስራዎች የጌጤኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ የጎርፍ መከላከያ ግብ ፕሮጀክት የቀላዳንባ ገበያ መአከል ግንባታ፣ ከሻሽ ጋራዥ- ቢራ መንድ ስራ፣ ከቀላዳንባ - ሙጢ መንገድ፣ የጀጎል ውስጥ ለውስጥ እና በጀጎል የሚገኙ የአስፓልት መንገገዶች የፅዳት ስራ፣ የሙከራ ትግበራ በጀጎል ውስጥ በ50 ሰራተኞች ሲሰራ የነበረው በ26 ሰዎች ተከናውኗል፡፡ የቀበሌ መዋቅራዊ ትስስርን ፈር ማስያዝ የሩብ አመቱ ዋንኛ አላማ ሲሆን ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከዋናው የስራ ሂደት አስከ ቀበሌ ያለው አገልግሎት ወጥነት ባለው መልኩ እንዲደራጁ የሚያስችል የክለሳ ሥራ መጠናቀቁን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ በ1ኛ ሩብ አመት ሊስበሰብ ከታቀደው ገቢ 632,538.00 ብር 736,436.73 መስብሰብና በአፈፃፀም ከእቅድ በላይ 16% መሆኑን በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ |
| |
![]() You are not logged in. |