.
Sunday, 20th May 2012
6:48:15pm
በሐረር ከተማ የሚደረጉ የICT እንቅስቃሴዎች በተመለከተ ሲፖዚየም ተካሂደ Print E-mail
Sunday, 06 December 2009 20:10
ህዳር 15/2002 ወረቀት አልባ በሚል መሪ ቃል በተደረገው ሲፖዚየም የሀረር ማዘጋጃ ቤትን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በዘርፉ እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ አቅርበዋል፡፡ የሀረር ማዘጋጃ ቤትም በICT ቴክኖሎጂ ዘርፍ  እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አቅርቧል።

የሐረር ማዘጋጃ ቤት ፤ በመሬት አስተዳደር፣ በገቢ ማስተዳደር፣ ንብረቶችንና እሴቶችን መቆጣጠር፣ በድረ-ገፅ ፣ የFTP እና Forum እንዲሁም በቀጥታ የድረ-ገፅ እንቅስቃሴዎች ማድረጉን በስፋት ያቀረበ ሲሆን የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ በበኩሉ የኤሌክትሮኒክስ ሜዲካል ሪከርድና ቴሌ ሜዲሲን የመሳሰሉ የ ICT ዘርፎች ላይ በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ላይ መሆኑን ገልፆአል ፡፡ የሀረሪ ክልል ፋይናንስ ቢሮም በIBEX የሂሳብ ገቢና ወጪ ገንዘቦች ላይ የተጠናከረ ስራን ለተገልጋዩ በማቅረብ ውጤት እንዳገኘ በሲንፖዚየሙ ላይ ቀርቧል፡፡

በዚህ ወደ ቴክኖሎጂ የመሸጋገርን ሁኔታ በሚያሣየው ሲንፖዚየም ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ረጋሳ ከፋለ በማንኛውም የስራ ዘርፍ ላይ ያለ ሰራተኛ ICTን መጠቀም እንዳለበትና የዘርፉን እድገት ለማጎልበት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ትልቅ ሚና መጫወት ያለባቸው የየመስራቤቶቹ ሀላፈዎች መሆናቸውን ገልፀው እንቅስቃሴያቸውን ባቀረቡት መስራቤቶች አበረታች ስራዎች መታየታቸው ጠቁመዋል፡፡

በሲምፖዚየሙ መጨረሻ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
 
HomeNewsGeneral News /  በሐረር ከተማ የሚደረጉ የICT እንቅስቃሴዎች በተመለከተ ሲፖዚየም ተካሂደ

 Site Visited

  98321 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM