.
Thursday, 23rd February 2012
3:12:36am
በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀረበ Print E-mail
Thursday, 20 May 2010 19:53

በመልካም አስተዳደር እና መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችለውን መሪ እቅድ በማዘጋጀት በከተማው ሁለንተናዊ እድገትና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጅምር ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የ2002 የዘጠኝ ወር ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በ2002 የዘጠኝ ወር ከተከናወኑ ስራዎች የጌጤኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ የጎርፍ መከላከያ ግብ ፕሮጀክት የቀላዳንባ ገበያ መአከል ግንባታ፣ ከሻሽ ጋራዥ- ቢራ መንድ ስራ፣ ከቀላዳንባ - ሙጢ መንገድ፣ የጀጎል ውስጥ ለውስጥ እና በጀጎል  የሚገኙ የአስፓልት መንገገዶች በአጠቃላይ የመንገዶች ሥራ ከ75% እስከ 95% ተከናውነዋል፡፡
 
 የፅዳት ስራ፣ የሙከራ ትግበራ በጀጎል ውስጥ በ50 ሰራተኞች ሲሰራ የነበረው በ26 ሰዎች ተከናወነ ሲሆን በሌላ በኩል ባለልኳንዳ ቤቶች በማህበር ተደራጅተው የቄራ አገልግሎት አሰጣጡን ደረጃ ለማሻሻል ብር 60,000.00 በሚገመት የክርስቲያን ቄራ እድሳት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡

የቀበሌ መዋቅራዊ ትስስርን ፈር ማስያዝ የዘጠኝ ወር ዋንኛ አላማ ሲሆን ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከዋናው የስራ ሂደት አስከ ቀበሌ ያለው አገልግሎት ወጥነት ባለው መልኩ እንዲደራጁ የሚያስችል የክለሳ ሥራ መጠናቀቁን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡


 የ2001 ዓ.ም የዘጠኝ ወር ገቢ ከ2002 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፃር የ2002 ገቢ 2,809,770.01  ብር ብልጫ ወይም በ32% የገቢ እድገት አሳይቷል፡፡

 
HomeNewsGeneral News /  በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የ2002 የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀረበ

 Site Visited

  82802 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM