|
በሐረር ከተማና በአከባቢዋ የሚገኙ ብርቅዬ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንዳይጠፉ በሀረር መዘጋጃ ቤት አስተባባሪነት የችግኝ ተከላ ተከናወነ |
|
|
|
Tuesday, 03 August 2010 14:40 |
|
ሀምሌ 2/ 2002 ዓ/ም በሀረር ከተማና በአከባቢዋ የሚገኙ ፍራፍሬዎችን በሚሊኒየም ፓርክ እዲተከሉ ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ ቀደምት ከተማ ከተመሰረቱ ጥቂት ከተሞች መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዷ የሆነችው ሀረር ለምስራቁ የሐገራችን ከፍል በጥንታዊ ታሪኳ የሃይማይኖት የንግድ የደጥበብ እና የመሳሰሉት ማዕከልነቷ ብቻ ሳይሆን በግብርና ሥራ በመስኖ በተለይም በአንቂና በፍራፍሬ ተክሎች ዝነኛና ለኢትዮጵያ ፈርጥ የነበረች ስለመሆኗ በታሪክ ድርሳናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲነገርላት ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ሰአት የምትታወቅበትን የፍራፍሬ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና ሃብቶቿን እንደነበረ ለማቆየት አለመቻሉ በዋናነት ሊጠቀስ ከሚችለው ምከንያት ባለፉት ሥርአቶች በልማቱ ትኩረት በመነፈጉና የህዝቧ ብዛት ከየትኛውም የሀገራችን ክፍል ባልተለመደ መልኩ መጨመሩ ባስከተለው መሰረታዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ችግሮች ሳቢያ ሀረር የአትክልት ፍራፍሬ አምራችነቷ ገፅታ ተለውጦ በአብዛኛው ከሌላ አካባቢ ማስመጣት ላይ ከመድረሷም አልፎ ብርቅዬ ፍራፍሬዎቿ እየጠፉ መሆኑ ታው ቋል ።
ከላይ የተጠቀሱትን የሀረርን መለያ እና መታወቂያ የሆኑትን የአትክልትና የተለያዩ የግብርና ሃብቶችን ወደ ነበረበረበት ቦታ ለመመለስ እና የሀረር ከተማ ገጽታ የመለወጥ እንቅስቃሴ አንዱ አድርጎ በዋነኝነት ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት በሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስተባባሪነት የክልሉ የግብርናና የገጠር መሰረተ ልማት ቢሮ ተባባሪነት እና የበጎ ፍቃደኛ በሆኑት በአቶ አሰፋ ፍሰሐ የፍራፍሬዎች ችግኝ አምራችነት እየጠፉ ያሉትን የሐረርን ፍራፍሬዎች መልሶ ለመትከል ማዘጋጃ ቤቱ እያለማ ባለው የሚሊንየም ፓርክ ላይ የተለያዩ የሀረር ነዋሪ የሆኑና እንዲሁ የማዘጋጃ ቤቱ ሰራተኞች የክልሉ የግብርናና የገጠር መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ጨምሮ በመሰብሰብ ታሪክ የማይረሳው አሪያ ሊሆን የሚችል ስራ ተከናውኗል።
በመጨረሻም በሀረር ብርቅዬ የሆኑ የፍራፍሬ ዝርያዎች እንዳይጠፉ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማቆየት መሰራት ካለበት ረጅም ጉዞ ውስጥ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነውን የችግኝ ተከላ እንዲሳካ ላደረጉት የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች የክልሉ የግብርና የገጠር መሬት ልማት ቢሮ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም በዋናነት የፍራፍሬ ችግኞች አፍርተው ችግኞችን ላበረከቱት የልማት አርበኛ ለሆኑት አቶ አሰፋ ፍሰሐ ትልቅ ምስጋና በሀረር መዘጋጃ ቤት ስም አቶ አብድላዚዝ ዬኒስ አቅርበዋል፡፡
|