.
Sunday, 20th May 2012
6:49:36pm
በሀረሪ/ክ/መንግስት የሀረር ማዘጋጃ ቤት የከተሞች መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ ጽ/ቤት ዘርፈ ብዙ የመሰረተ ልማት ሰራዎች ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ Print E-mail
Tuesday, 08 December 2009 20:24
በከተማዋ በመሰራት ላይ ካሉት 12 ፕሮጀክቶቸ ውስጥ አንዱ ለደራሽ ጎርፍ አደጋ እና ስጋት በተጋለጡ መንደሮች ውስጥ ባሉ ወንዞቸ ላይ የጎርፍ መከላከያ ግንብ ግንባታ ፕሮጀክት (FLOOD PROTECTION RETAINING WALL PROJECT) አንዱ ነው:: በሁለት ቀበሌ መሰተዳድሮቸ ውስጥ የተሰሩ የጎርፍ መከላከያ ግንቦች የተጠናቀቁ ሲሆን በጎርፍ ስጋት ተጨንቆ የነበረው ነዋሪ ህብረተሰብም ደስታውን ገልጾ መንግስት እየተገበረ በሚገኘው የልማት አቅጣጫ ለመሳተፍ ያለውን ተነሳሽነት ገለጿል::
   
በታሪካዊው የጀጎል ግነብ ዙሪያ እየተሰራ ያለው የኮብልስቶን መንገድ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል::
በታሪካዊው የጀጎል ግነብ ዙሪያ እየተሰራ ያለው የኮብልስቶን መንገድ ስራ ከአስሱም በሪ (ከፈላና በር) እስከ ሱጉድ አጥ በሪ(ሰንጋበር) ያለው የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም ከበድሮ በሪ (ቡዳ በር) እስክ አስመአዲን በሪ (ሸዋ በር) ድረስ ያለውን መንገድ በኮበል ስቶን የማንጠፍ ሳራው ተጀምሮ በመከናወን ላይ ይገኛል::በማሰተባበሪያ ጽ/ቤቱ በኩል ተደራጅተው በኮብልእስቶን ጠረባ እና ንጣፍ ስራ ላይ የተሰማሩ መሐበራት በአጠቃላይ 51 መሀበራት ሲሆኑ ይህም ቁጥራቸው 1200 ለሚበልጡ እና በተለያየ የእድሜ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እድል ከፍቷል:: ከዚህ በተጨማሪም በንጣፍ ስራ ከቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በኮብልስቶን ጠረባ እና ንጣፍ የተመረቁ በቁጥር 180 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገ ኛሉ ::
በአጠቃላይ ከሀምሌ2001 ዓ/ም እስከ ህዳር 2002 ድረስ በቁጥር 1274824 ጌጠኛ ድንጋዮች የተመረቱ ሲሆን ለዚህም ብር 3569507.20 በስራ ለመሀበራቱ ተከፍሏል::
   
 
HomeNewsProject News /  በሀረሪ/ክ/መንግስት የሀረር ማዘጋጃ ቤት የከተሞች መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፋፊያ ጽ/ቤት ዘርፈ ብዙ የመሰረተ ልማት ሰራዎች ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

 Site Visited

  98324 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM