.
Thursday, 23rd February 2012
3:14:50am
በ4ኛ ፈዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ ምክንያት በመንገድ ግራና ቀኝ የሚነሱ ዜጎች ያለመንግስት ተፅእኖ የመኖሪያ ቤታቸውንና የንግድ ቤታቸውን እያፈረሱ መሆናቸውን ገለፁ፡፡ Print E-mail
Thursday, 11 February 2010 17:31

ጥር 26,2002 ዓ/ም የመጀመሪያ አፍራሽ የነበሩት የአራተኛ እድገት በር የንግድ ህንፃ አሰሪ ማህበር የሆኑት ሊቀመንበር ሻምበል ማሞ መታፈሪያ እንዲሁም የማህበሩ ሂሳብ ያዥ የሆኑት አቶ ዳንኤል እና የማህበሩ አባል የሆኑት አቶ መላከ ማንጉዳይ የወፍጮ ቤታቸውን ጣሪያና እንዲሁም መሰል የንግድ መደብራቸውን በማፍረስ ላይ መሆናቸውን በቦታው ላይ ሆነን ከማየታችንም በላይ ቃለ-መጠይቅ ያደረግንላቸው ሲሆን ለማፍረስ ያነሳሳቸው ምክንያት ሲጠቅሱ የክልሉ መንግስት ከሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጋር ሆኖ ያደረገልን ካሳ እንዲሁም ምትክ ቦታዎች ከጠበቅነው በላይ ስላደረገልንና በተጨማሪም ለህብረተሰቡ ቀዳሚ ሆነን ለማሳየትና ከልማቱ በቀጥታ ተሳታፊ መሆናቸው ለማስገንዘብ ስላስፈለጉ እንደሆነ ገልፀውልናል፡፡
ሻምበል ማሞ መታፈሪያ
አቶ  መላከ አቶ ዳንኤል
.
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሌሎች ከማህበሩ ውጪ የሆኑና በመንገድ መሰራት ምክንያት ተነሺ የሆኑ ሰዎች በቀዳሚነት የማፍረስ ሂደቱን አጠናቀው በግልፅ የወጣውን የምትክ ቦታ እጣ በቦታቸው ለመረከብ ዝግጅታቸውን አጠናቀው መሰል የስራ አጋሮቻቸውን የማፍረስ ሂደቱን ከተሰጠው የጊዜ ቀነ ገደብ በፊት እንዲያጠናቅቁ እገዛ እያደረጉላቸው መሆኑን ተናግረዎል፡፡
 
HomeNewsProject News /  በ4ኛ ፈዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ ምክንያት በመንገድ ግራና ቀኝ የሚነሱ ዜጎች ያለመንግስት ተፅእኖ የመኖሪያ ቤታቸውንና የንግድ ቤታቸውን እያፈረሱ መሆናቸውን ገለፁ፡፡

 Site Visited

  82807 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM