.
Thursday, 23rd February 2012
3:13:00am
የአራተኛ ፈዲስ መሰመር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ኘሮጀከት ቅድመ ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡ Print E-mail
Friday, 19 February 2010 17:58
የአራተኛ ፈዲስ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የቅድመ ግንባታ እንቅስቃሴ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ የቅድመ ግንባታ እንቅስቃሴው ህብረተሰቡንና የሚመለከታቸው አካላት ባሳተፈ መልኩ በተለያየ ጊዜ ከአካባቢው ህብረተሰብና ከህብረተሰቡ የተውጣጡ የተለያዩ ኮሚቴዎች ጋር በተደጋጋሚ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን የህብረተሰቡ ተወካይ ኮሚቴዎችና ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጡ ግብረ-ሀይሎች አማካይነት አስፈላጊ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ ተደርጓል፡፡

በአስፋልት ግንባታው ሳቢያ ለሚነሱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ የገበያ ስፍራ ሲዘጋጅ መኖሪያ ቤታቸው የሚፈርስባቸው የመንገድ ግራና ቀኝ ነዋሪዎች ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተዘጋጅቷል፡፡
   
የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሐረር ፈዲስ ትራንስፖርት አገልግሎትም እንዳይስተጓጎል ተለዋጭ መንገዶች ተዘጋጅቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከአካባቢው ለሚነሱ ህብረተሰብ የካሳ ክፍያ እየተፋጠነ ሲሆን እነዚህን ነዋሪዎችና ነጋዴዎች በመንገዱ ግራና ቀኝ የነበሩትን ቤቶች በማፍረስ ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ ለማሸጋገር ( ርክክብ ለማድረግ) አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም እስካሁን ድረስ የሚመለከታቸው አካላትና ህብረተሰቡ ያሳየው በጎ አመለካከት ፣ትብብርና ድጋፍ እያመሰገንን ለከተማችን እድገት መፋጠን የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለሚያከናውናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
 
HomeNewsProject News /  የአራተኛ ፈዲስ መሰመር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ኘሮጀከት ቅድመ ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡

 Site Visited

  82803 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM