| በአራተኛ ፈዲስ አስፓልት መንገድ ኘሮጀክት ምክኒያት 380 የንግድ የመኖሪያ ቤቶች ለፈረሰባቸው 9.8 ሚሊዩን ብር ካሳ ተከፈለ |
|
|
| Saturday, 13 February 2010 17:47 | ||||||||
|
በአራተኛ ፈዲስ አስፓልት መንገድ ኘሮጀክት እስከ አሁን 380 በአከባቢው የሚገኙ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች መፍረሳቸውን የሐረር ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ ፡፡
የሐረር ከተማ የካቢኔ አባላት በተገኙበት ሪፖርታቸውን ያቀረቡት አቶ ተወለዳ አብዳሽ እንደገለፁት በአራተኛ ፈዲስ የአስፓልት ኘሮጀክት 380 የንግድና የመኖሪያ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን ከነዚህ መሃል 52 መኖሪያ ቤቶች 322 የንግድ ቤቶች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የንግድና የመኖሪያ ቤት ባለቤቶች ተገቢውን ካሳ ተከፍሏቸው በተወሰደባቸው መሬት ምትክ የንግድና የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተሰጧቸዋል፡፡
በመንገድ መገንባት ምክኒያት የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች የከተማው ሹም ሲጠቅሱ 322 የንግድ 52 መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ 22 አርሶ አደሮች ከይዞታቸው እንዲነሱ መደረጉን ጠቅሰው ለእያንዳንድ ተነሺ ተገቢውን የካሳ ክፍያ መስጠቱ ተናግረዋል፡፡ በመንገድ ግረና ቀኝ የመልሶ ማልማቱ እንቅስቃሴ የተሳካ እንዲሆን ለአከባቢው በግል ባለሃብቶች ተይዞ ለልማት ሳይውል የቀረን ቦታ እና በአራት ባለሃብቶች ተይዞ የነበረ 8580 ካሬ ሜትር በልማት እንድውል የሐረር ማዘጋጃ ቤት መረከቡን ለካቢኔ አባላቶች አሳውቀዋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው ጋር በተያያዘ በአራተኛ ፈዲስ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ወቅት በተለዋጭ መንግድ ግንባታ የሚያስፈልግ መሬት የማልማት ሥራ ጎን ለጎን በሳንፊል ጀርባ ለህገወጥ የመሬት ሽያጭ የተጋለጠቀውን 5.5 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን ዓመታውና ቋሚ ተክል ግምት ተርቶ ለ13 ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ተከፍሎ ይዞታው በማዘጋጃ ቤቱ ስር እንዲውል መደረጉ የከተማው ሥራ እስኪያጅ ገልፀዋል፡፡
የሐረር ከተማ ሥራ አስኪያጅ ያቀረቡት የ2002 ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአራተኛ ፈዲስ መንገድ አከባቢ በማዘጋጃ ቤቱ በULGDP ለሚገንባው የገበያ ማአከል 440 ካ/ሜ ቦታ ከመዘጋጀቱም በላይ የመሬት ይዞታቸውን የተነጠቁ ባለሃብቶች ባቀረቡት ኘሮጀክት መሰረት በዋናው መንገድ ላይ 500 እስከ 600 ካ/ሜ ቦታ ላይ የአከባቢውን ደረጃ የጠበቀ ለንግድ አገልግሎት የሚውል ህንፃ እንዲገነቡ ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በአራተኛ ፈዲስ በአዲስ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ኘሮጀክቱን ለመስራት ውሉን የፈረመው የቻይና ኩባንያ ስራውን መጀመሩን ታውቀዋል፡፡ |
| |
![]() You are not logged in. |