|
የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ለመሰብሰብና ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ማዘጋጃ ቤቱ አስታወቀ፡፡ |
|
|
|
Friday, 02 April 2010 19:45 |
|
በሀረር ከተማ ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ከእያዳንዱ መኖሪያ ቤት የሚወጣውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ የመሰብሰብና የማስወገድ ስራ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በከተማዋ በአሁኑ ወቅት ከ50 በመቶ በታች ደረቅ ቆሻሻ ብቻ ነው በአግባቡ የሚወገደው፡፡ ይህን ለተለያየ ተላላፊ በሽታዎች አጋላጭ የሆነውን የደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ለመሰብሰብ፣ ለመያዝና ለማሰወገድ በ6 ማህበር ለተደራጁ ስራ አጦች የሀረሪ ክልል ተቋማት ልማትና የስራ እድል ፈጠራ ድጋፍ አሰጣጥ የስራ ሂደት በ8 ቀናት የቆየ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ በሀረር ከተማ ከሚገኙ 6ቱም የአካባቢ ቀበሌ መስተዳድሮች የተወጣጡ 89 ስራ አጦች የተካፈሉበት ሲሆን በቆይታቸውም ቆሻሻን እንዴት መለየት፣ማጓጓዝ እንደሚቻል እንዲሁም የሂሳብ መዝገብ አያያዝና ስነ-ምግባር በሚሉ ርዕሶች ስልጠናው ተሰጥቷቿዋል፡፡ ለሰልጣኞች የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት የሰጡት በሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የማበራዊና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልአዚዝ ዩኒስ ባደረጉት ንግግር ማዘጋጃ ቤቱ በሀረር ከተማ ለውጥ ለማምጣት በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ማ/ቤቱ በከተማው ውስጥ የሚስተዋለውን የደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ መሰብሰብና ማስወገድ አንዲቻል ማስፈፀሚያ ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን የጠቆሙት አቶ አብዱልዚዝ ቆሻሻ ሃብት በመሆኑ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻልና ከየቤቱ የሚወጣውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ማስወገድ እንድትችሉ ከአካባቢ ቀበሌ መስተዳደሮች ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እገዛ ይደረግላችኋል ብለዋል፡፡
አቶ ፀጋዬ ለገሠ በተቋማት ልማትና የስራ እድል ፈጠራ ድጋፍ አሰጣጥ የስራ ሂደት የአደረጃጀት ኦፊሰር በበኩላቸው የስራ ሂደቱ በከተማው የሚሰተዋውን የስራ አጥነት ችግር ለማስወገድ ስራ አጦች በበቂ እውቀት የስራ እድል እንዲያገኙ በስልጠና፣ በምክር አገልግሎትና በሌሎችም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀው በየአካባቢው የሚስተዋለውን የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣አያያዝና አወጋገድ ላይ በማህበር እንዲደራጁ ስልጠና ከመሰጠቱም ባሻገር ሁኔታዎች ማመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡
ስልጣኞች በስምንት ቀን የስልጠና ቆይታቸውን ከንድፊ ሃሳብ በተጨማሪ ላይ የተግባር ልምምድ ያደረጉ ሲሆን በስልጠናውም በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸው ስራ በሚጀምሩበት ወቅት ህብረተሰቡን በአገልግሎታቸው ጠቅመው በገቢም ራሳቸውን ሊጠቅሙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡ የሀረር ክልል የተቋማት ልማትና የስራ እድል ፈጠራ ድጋፍ አሰጣጥ የስራ ሂደት ለስልጣኞች ስራ ማሰጀመሪያ የሚሆን ግምቱ ከ27 ሺህ ብር በላይ የሆነ የደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ፣መያዢያና ማስወገጃ ማሣሪያዎችን ለየማህበራቱ አሰረክቧል፡፡
|