.
Thursday, 23rd February 2012
3:15:17am
የደረቅ ቆሻሻ አሰባበሰብና አወጋገድ ሥራዓትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ Print E-mail
Thursday, 18 February 2010 17:22
ቀደም ሲል የሐረር ከተማ ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰቢያና ማስወገጃ ቦታ በመታፈሪያ አማካሪ ኢንጂነሮች ድርጅቶች አማካኝነት ተጠንቶ በደከር መሥመር ልዩ ሥሙ ጩርጩራ የሚባል አከባቢ ተመራጦ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ቦታ በርካታ አርሶ አደሮች የሚኖሩበት እንዲሁም የሐረር ከተማ ማስፋፊያ አካባቢ /Expansion area/ ከመሆኑም በላይ በግምት 400 ቤተሰቦች ሊሰፍሩበት ከተዘጋጀው (LDP) መሬት በ200 ሜትር ርቀት የሚገኝ ነው፡፡

በሌላ በኩል ከከተማዋ የሚወጣው ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰቢያና ማስወገጃ ስፍራ በስታንዳርዱ መሰረት ከከተማ ቢያንስ 5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መዘጋጀት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቀደም ሲል በአማካሪ ድርጅቱ የተመረጠው ቦታ ይህንን ስታንዳርድ ያሟላ አልነበረም፡፡

ስለሆነም የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ይህንን ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ እንዲሁም ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር በመሆን ልዩ ስሙ ጩርጩራ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ከ2-3 ኪሜ ርቀት የሚገኝ ስፍራ በመምረጥ የአካባቢ ተፅእኖ ዳሰሳ /Enviromental impact Assessment/ ጥናትን በተመለከተ አማካሪ ድርጅቱ የከርሰ ምድር ጥናት፣የአፈር ጥናት እንዲሁም ሌሎችን ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥናቶችን እንዲያጠና ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
   
 
HomeNewsServices News /  የደረቅ ቆሻሻ አሰባበሰብና አወጋገድ ሥራዓትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

 Site Visited

  82808 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM