.
Thursday, 23rd February 2012
3:12:08am
በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አንድ አባል የሆነው መሀበራዊ ኤጀንሲ በኩል በደረቅ ቁሻሻ አሰባሰብ አወጋገድ እና ከከተማው በሚሰበስበው ቁሻሻ የተፈጥሮ የእርሻ ማዳበሪያ የሚያዘጋጅ14 መሃበራት ተደራጁ፡፡ Print E-mail
Monday, 08 March 2010 19:49

  በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት መሀበራዊ ኤጀንሲ በኩል የከተማችን ደረቅ ቁሻሻ ለማሰባሰብና ለማስወገድ እንዲቻል ከተቋቋሙት መሃበሮት  መሃል 12 መሃበሮች በደረቅ ቁሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ሥራ ላይ የሚሰማሩ ሲሆን የህብረት ሥራ ማሀበራት ሲደራጁ ከእንያንዳንዱ ቀበሌ መስተዳደር ሁለት ነዋሪዎችን ያቀፈና በያንዳንዱ በሀበር ውስጥ 20 ሥራ አጥ ወጣቶች ሲኖሩ በድምሩ ለ240 ሰዎች የሥራ እድል ፈጥሮአል ፡፡


  እነዚህ ነሀበራት ለዚህ ስራ ላይ ሲሰማሩ የከተማችንን ፅዳት ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ተገልፃል ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሐረር ከተማ ከየቀበሌው ከሚሰበሰበው ደረቅ እና በስባሽ የእርሻ ማዳበሪያ የሚያዘጋጁ ሁለት መሃበራት በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ማህበራዊ ኤጀንሴ በኩል ተደራጅተዋል ፡፡ ሁለቱ መሀበራት እያንዳንዱ 12 ሥራ አጥ ወጣቶችን ሲይዙ በአጠቃላይ ለ24 ስራ አጥ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ቁሻሻን እንዳስፈላጊነቱ ለይቶ ለተለያዩ ጥቅሞች ከማዋል አንፃር በተለይም ከቁሻሻ የእርሻ ማዳበሪያ በማዘጋጀት ለምርታማነት አስተዋፅኦ ማበርከቱ ድህንነቱ ለመቅረፍ ከተያዝነው የልማት ስራትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ተምሮበታል ፡፡


  በመጨረሻም ደረቅ ቁሻሻ አሰባሰብ አወጋገድ ለተሰማሩትና እንደዚሁም በቁሻሻ የተፈጠሮ ማዳበሪያ የሚያዘጋጁት መሃበራት አስፈላጊውን ስልጠና  ከተሰጣቸው በኃላ በቀጣዩ ጊዜያት ስራቸውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ፡፡

 

 
HomeNewsServices News /  በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አንድ አባል የሆነው መሀበራዊ ኤጀንሲ በኩል በደረቅ ቁሻሻ አሰባሰብ አወጋገድ እና ከከተማው በሚሰበስበው ቁሻሻ የተፈጥሮ የእርሻ ማዳበሪያ የሚያዘጋጅ14 መሃበራት ተደራጁ፡፡

 Site Visited

  82801 times

Copyright © 2012. Harar Municipality.                 Designed by Binyam TM